Various Amharic Letter Templates

Resourceful page where you can find sample Amharic legal, business, wedding and professional letters.

Ethiopian Wedding Invitations - የሰርግ ጥሪ
Ethiopian Post-Wedding Invitations - የመልስ ጥሪ
Memorial Services for 40 and 80 days mark - የተስካር ጥሪ
Ethiopian Power of Attorney - የውክልና ስልጣን ማስረጃ



Ethiopian Wedding Invitations - የሰርግ ጥሪ
Traditional Ethiopian wedding ceremony invitation letter.

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የልጃችን
የወ/ሪት __________
እና
የአቶ __________

የሠርግ ሥነ-ሥርዓት የሚፈፀመው ዕሁድ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ7:00 ሰዓት ላይ ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ ባለው አዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀነው የምሳ ግብዣ ላይ ከ __________ ጋር እንዲገኙልን በማክበር ጠርተኖታል።

ወ/ሮ _________
አድራሻ : ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ ባለው የቀበሌ 08 አዳራሽ ውስጥ


Ethiopian Post-Wedding Invitations - የመልስ ጥሪ
Traditional post wedding invitation letter for two couples celebrating at the same time.

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የልጆቻችንን
የወ/ሎ ________          የወ/ሎ ________
እና       እና       እና
የአቶ ________          የአቶ ________

የመልስ ሥነ-ስርዓት ቅዳሜ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም ስለሆነ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት በመኖሪያ ቤታችን በምናደርገው የምሳ ግብዣ ላይ ከ __________ ጋር እንዲገኙልን በማክበር ጠርተኖታል።

ወ/ሮ _________
አድራሻ : ከቀዩ በር ጎን


Memorial Services for 40 and 80 days mark - የተስካር ጥሪ
Sample Ethiopian memorial services invitation letter to mark 40th and 80th days .

የ ፰ ቀን መታሰቢያ

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን

የሐዘናችን ተካፋይ ለሆናችሁ የልጄ __________ የ 80 ቀን መታሳቢያ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2012 ዓ.ም ስለሆነ እርሶም በዚሁ ቀን በ7:00 ሰዓት ፀበል ፃዲቁን እንዲቀምሱልን በማክበር ከ __________ ጋር ጠርተንዎታል።

ጠሪ

ደበበ ካሳ

አድራሻ : ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ



Ethiopian Power of Attorney - የውክልና ስልጣን ማስረጃ
This free sample of Ethiopian power of attorney statement contains a wide range of authorities the applicant wishes to delegate to the agent. It's always best to first consult with your lawyer before delegating someone. Ethiopian power of attorney in Amharic.

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም
የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

የውክልና ስልጣን ማስረጃ

ወካይ → አቶ አበበ በቀለ ግርማ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/

አድራሻ : አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 251

ተወካይ → አቶ በቀለ ግርማ ቦጋለ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/

አድራሻ : አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 125


እኔ ወካይ ለተወካይ አባቴ የምሰጣቸው የውክልና ስልጣን በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውንና ወደፊት የሚመዘገበውን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በተመለከተ ተወካይ እንደ እኔ በመሆን እንዲጠብቁ ፤ እንዲቆጣጠሩ እንዲያስተዳድሩ ፤ እንዲሸጡ እንዲለውጡ ፤ ስም እንዲያዛውሩ ፣ ገንዘብ እና ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ ፣ ግብርም ሁነ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ፣ እንዲያከራዩ ፣ እንዲኮናትሩ ፣ የኪራይ ውል እንዲዋዋሉ እና ውሉንም እንዲያፈርሱ ፣ በስሜ በማህበርም ሆነ በሊዝ በግል ለኢንቨስትመንት ለመኖሪያ ቤትም ሆነ ለድርጅት መስሪያ የሚሆን ቦታ እንዲረከቡ ፣ ካርታ ፤ ፕላን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ፈርመው እንዲቀበሉ ፣ የግንባታ ፈቃድ እና የፕላን ማሻሻያ እንዲያወጡ ፣ የግንባታ ስራዎችን ባለሙያ ቀጥረው ግንባታ እንዲያካሂዱ ፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ማቴሪያል /ሲሚንቶ/ እንዲገዙ ፣ ስልክ ፤ ውኃ ፤ መብራት እንዲያስገቡ ፣ በስሜ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያወጡ ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውል እንዲያድሱ ፣ በስሜ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲገዙ ፣ ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ ፣ ቦሎ ከላውዶ እንዲያስደርጉ ፣ ሰሌዳ እንዲያስለጥፉ ፣ ታርጋ እንዲያወጡ ፣ በስሜ አዲስ የባንክ ሂሳብ ከፍተው ገንዘብ ገቢና ወጪ እንዲያደርጉ ፣ ከዚህ በፊት የተከፈተውንም እንዲያንቀሳቅሱ ፣ ገንዘብ ገቢና ወጪ እንዲያደርጉ ፣ ቼክ ላይ እንዲፈርሙ ፣ ቼክ እንዲመነዝሩ ፣ ቼክ እንዲያውጡ ፣ ማንኛውንም ንብረቴን በዋስትና በማስያዝ ገንዘብ ከባንክም ሆነ ከአበዳሪ ድርጅቶች እንዲሁም ከግለሰብ መበደርም ሆነ ማበደር እንዲችሉ ፣ ዋስ እንዲሆኑ ፣ ተሳስበው እንዲከፍሉ ፣ የማስመጣትና የመላክ የንግድ ስራ በስሜ እንዲያከናውኑ ፣ በስሜ ንግድ ፈቃድ እንዲያወጡ ፣ ፈቃድ እንዲያስድሱ ፣ የንግድ ስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ ፣ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው ንግድ ፈቃዱን እንዲመልሱ ፣ ከውጪ ሃገር በስሜ ተመዝግቦ የሚመጣውን ማንኛውንም እቃም ሆነ መኪና አስፈላጊውን የጉምሩክ ፎርማሊቲዎችን አሟልተው እንዲረከቡ ፣ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ፣ ሰነድ እንዲቀበሉ /ዶክመንቶች/ እንዲቀበሉ ፣ ሊብሬ እንዲያወጡ ፣ ሰሌዳ እንዲያስለጥፉ ፣ መንግስታዊ ክፍያዎች እንዲከፍሉ ፣ ማስረጃ እንዲሰጡ እንዲቀበሉ ፣ ለማንኛውም ንብረቴ ኢንሹራንስ እንዲገቡ ፣ የኢንሹራንስ ካሳ ክፍያ ገንዘብ እንዲቀበሉ እንዲዋዋሉ እና ሰነድ እንዲፈርሙ ፣ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና እንዲቀበሉ ፣ ከመንግስት አካልም ሆነ ከግለሰብ እንዲሁም ከግል ድርጅት ሰነድ እንዲፈርሙ ገንዘብ እንዲከፍሉ እና እንዲቀበሉ ፣ ከመንግስት አካልም ሆነ ከግለሰብ እንዲሁም ከግል ድርጅት ማግኝት የሚገባኝን ማንኛውም ገንዘብም ሆነ ጥቅማ ጥቅም አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው ውል በመዋዋል እንዲቀበሉልኝ ፣ ማንኛውንም ውል እንዲዋዋሉ ፣ ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ ፣ የስምምነት ውል እንዲዋዋሉ ፣ በውርስም ሆነ በስጦታ የማገኝውን ንብረት እንዲረከቡልኝ ፣ ወደስሜ እንዲያዛውሩ ፣ ከማንኝውም የትምህርት ተቋም ያሉኝን የትምህርት ማስረጃዎች ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉልኝ ፣ አክሲዮንም ሆነ ኩባንያ በስሜ እንዲያቋቁሙ ፣ በስብሰባ እንዲሰበሰ ቡ ፣ በቃለ ጉባዔ በመተዳደሪያ በመመስረቻ ጽሁፍ ላይ እንዲፈርሙ ፣ የአክሲዮንም ሆነ የኪባንያ ድርሻዬን እንዲቀበሉ እንዲሸጡ እንዲለውጡ ፣ የጨረታ ሰነድ እንዲገዙ ፣ ጨረታ እንዲጫረቱ ፣ ተመላሽ ሂሳብ እንዲቀበሉ ፣ ሪፖርት እንዲያደርጉ ፣ ሲፒኦ እንዲሰሩ እንዲያስይዙና የተያዘውን ሲፒኦ እንዲያስመልሱ ፣ ክሊራንስ እንዲያመጡ ፣ የቫት ክፍያ እንዲከፍሉ ፣ በመንግስታዊ መ/ቤትም ሆነ ህዝባዊያን ድርጅት የግል መ/ቤት አስተዳደር መ/ቤት በአገር ውስጥ ገቢ በንግድና ኢንድስትሪ በኢንቨስትመንት ቢሮ በመብራት ኃይል በቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሞባይል መምሪያና በውሃና ፍሳሽ መ/ቤቶች በቀበሌ በክ/ከተማ በመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ በኤምግሬሽን በውጭ ጉዳይ በኤምባሲዎች በማዘጋጃ ቤት በመቅረብ ውል እንዲዋዋሉና እንዲድሱ ፣ በፖስታ ቤት አገልግሎት በስሜ የሚመጣውን ማንኛውንም ዕቃም ሆነ ሰነዶች እንደ እኔ ሆነው ፈርመው እንዲረከቡ ፣ በኢምግሬሽን መ/ቤት በቤቶች ልማት ኤጀንሲ ዘንድ እኔ ቀርቤ መፈፀም እና ማስፈፀም የሚገባኝን ጉዳዮች ተከታትልው እንዲፈጽሙ እና እንዲያስፈጽሙ ፣ በምከሰስበትም ሆነ በምከስበት ጉዳይ ላይ ቢችሉ ራሳቸው ባይችሉ የህግ ጥበቃ ወክለው እንዲከራከሩ መልስ እንዲሰጡ ቃለ መሀላ እንዲያቀርቡ አፈፃፅም እንዲከታተሉ ማረጋገጫ እንዲፈርሙ ይግባኝ እንዲጠይቁ ውሳኔ እንዲቀበሉ የእርቅ ስምምነት እንዲያደርጉ ፣ በፍርድ የሚሰጠኝን ማንኛውንም ንብረትም ሆነ ገንዘብ እንዲቀበሉ ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሌላ ሶስተኛ ውገን መወከልም ሆነ መሻር እንዲችሉ ፣ ይህንን ሙሉ የውክልና ሥልጣን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2199/2205 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ 58 መሠረት መስጠቴን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ።

የወካይ ሙሉ ስም


የወካይ ፊርማ



Connect with us!

MetaAppz Facebook Page MetaAppz Twitter Page MetaAppz Pinterest Page MetaAppz Youtube Page