Explore a rich collection of Amharic proverbs that reflect the wisdom and cultural heritage of Ethiopia. Our collection includes a wide range of common proverbs, each with its unique meaning and context. You can easily browse the proverbs alphabetically or search for a specific one using your own keywords. Whether you are a language enthusiast, a student of Amharic culture, or simply looking for inspiration, our collection of Amharic proverbs is an excellent resource to explore. Start browsing now and discover the beauty and richness of Amharic language and culture. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ነገር ስንት ነው ሁለት ምን ያበዛዋል ውሽት ነገር በሆዴ መንገድ በአመዴ ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ ነገር በለዛው ጥሬ በለዛዛው ነገር በልክ ሙያ በልብ ነገር በመልከኛ ጠላ በመክደኛ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ መዝሙር በሀሌ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ዜማ በሀሌ ነገር በቀጠሮ ዘፈን በከበሮ ነገር በትኩሱ ጨዋታ በወዙ ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ ነገር በእርቅ ወይፈንን በድርቅ ነገር በወቀሳ በደል በካሳ ነገር በዋስ እህል በነፋስ ነገር በዋና ሚዶ በእረኛ ነገር በዋና ሜዳ በአረና ነገር በዋና ዘፈን በገና ነገር በዋናው ንብ በኣውራው Previous12345678910Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra