Various Amharic Letter Templates

Resourceful page where you can find sample Amharic legal, business, wedding and professional letters.

Traditional Ethiopian wedding ceremony invitation letter.

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የልጃችን

የወ/ሪት __________

እና

የአቶ __________

የሠርግ ሥነ-ሥርዓት የሚፈፀመው ዕሁድ ጥር 20 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ7:00 ሰዓት ላይ ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ ባለው አዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀነው የምሳ ግብዣ ላይ ከ __________ ጋር እንዲገኙልን በማክበር ጠርተኖታል።

ወ/ሮ _________

አድራሻ : ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ ባለው የቀበሌ 08 አዳራሽ ውስጥ

Traditional post wedding invitation letter for two couples celebrating at the same time.

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የልጆቻችንን

የወ/ሪት ________          የወ/ሪት ________

እና       እና       እና

የአቶ ________          የአቶ ________

የመልስ ሥነ-ስርዓት ቅዳሜ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም ስለሆነ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:00 ሰዓት በመኖሪያ ቤታችን በምናደርገው የምሳ ግብዣ ላይ ከ __________ ጋር እንዲገኙልን በማክበር ጠርተኖታል።

ወ/ሮ _________

አድራሻ : ከቀዩ በር ጎን

Sample Ethiopian memorial services invitation letter to mark 40th and 80th days.

የ ፰ ቀን መታሰቢያ

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን

የሐዘናችን ተካፋይ ለሆናችሁ የልጄ __________ የ 80 ቀን መታሳቢያ ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2012 ዓ.ም ስለሆነ እርሶም በዚሁ ቀን በ7:00 ሰዓት ፀበል ፃዲቁን እንዲቀምሱልን በማክበር ጠርተኖታል።

ጠሪ

ደበበ ካሳ

አድራሻ : ከሽሮ ሜዳ ገበያ ጀርባ

This free sample of Ethiopian power of attorney statement contains a wide range of authorities the applicant wishes to delegate to the agent. It's always best to first consult with your lawyer before delegating someone. Ethiopian power of attorney in Amharic.

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትህ ሚኒስቴር ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም

የሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት

አዲስ አበባ

የውክልና ስልጣን ማስረጃ

ወካይ → አቶ አበበ በቀለ ግርማ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/
አድራሻ : አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 የቤት ቁጥር 251

ተወካይ → አቶ በቀለ ግርማ ቦጋለ /ዜግነት ኢትዮጵያዊ/
አድራሻ : አ.አ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 የቤት ቁጥር 125

እኔ ወካይ ለተወካይ አባቴ የምሰጣቸው የውክልና ስልጣን በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘውንና ወደፊት የሚመዘገበውን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በተመለከተ ተወካይ እንደ እኔ በመሆን እንዲጠብቁ ፤ እንዲቆጣጠሩ እንዲያስተዳድሩ ፤ እንዲሸጡ እንዲለውጡ ፤ ስም እንዲያዛውሩ ፣ ገንዘብ እና ሰነድ ፈርመው እንዲቀበሉ ፣ ግብርም ሁነ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ፣ እንዲያከራዩ ፣ እንዲኮናትሩ ፣ የኪራይ ውል እንዲዋዋሉ እና ውሉንም እንዲያፈርሱ ፣ በስሜ በማህበርም ሆነ በሊዝ በግል ለኢንቨስትመንት ለመኖሪያ ቤትም ሆነ ለድርጅት መስሪያ የሚሆን ቦታ እንዲረከቡ ፣ ካርታ ፤ ፕላን የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ፈርመው እንዲቀበሉ ፣ የግንባታ ፈቃድ እና የፕላን ማሻሻያ እንዲያወጡ ፣ የግንባታ ስራዎችን ባለሙያ ቀጥረው ግንባታ እንዲያካሂዱ ፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ማቴሪያል (ሲሚንቶ) እንዲገዙ ፣ ስልክ ፤ ውኃ ፤ መብራት እንዲያስገቡ ፣ በስሜ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያወጡ ፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውል እንዲያድሱ ፣ በስሜ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እንዲገዙ ፣ ወደ ስሜ እንዲያዛውሩ ፣ ቦሎ ከላውዶ እንዲያስደርጉ ፣ ሰሌዳ እንዲያስለጥፉ ፣ ታርጋ እንዲያወጡ ፣ በስሜ አዲስ የባንክ ሂሳብ ከፍተው ገንዘብ ገቢና ወጪ እንዲያደርጉ ፣ ከዚህ በፊት የተከፈተውንም እንዲያንቀሳቅሱ ፣ ገንዘብ ገቢና ወጪ እንዲያደርጉ ፣ ቼክ ላይ እንዲፈርሙ ፣ ቼክ እንዲመነዝሩ ፣ ቼክ እንዲያውጡ ፣ ማንኛውንም ንብረቴን በዋስትና በማስያዝ ገንዘብ ከባንክም ሆነ ከአበዳሪ ድርጅቶች እንዲሁም ከግለሰብ መበደርም ሆነ ማበደር እንዲችሉ ፣ ዋስ እንዲሆኑ ፣ ተሳስበው እንዲከፍሉ ፣ የማስመጣትና የመላክ የንግድ ስራ በስሜ እንዲያከናውኑ ፣ በስሜ ንግድ ፈቃድ እንዲያወጡ ፣ ፈቃድ እንዲያስድሱ ፣ የንግድ ስራ ዘርፍ እንዲቀይሩ ፣ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልተው ንግድ ፈቃዱን እንዲመልሱ ፣ ከውጪ ሃገር በስሜ ተመዝግቦ የሚመጣውን ማንኛውንም እቃም ሆነ መኪና አስፈላጊውን የጉምሩክ ፎርማሊቲዎችን አሟልተው እንዲረከቡ ፣ ሰነድ ላይ እንዲፈርሙ ፣ ሰነድ እንዲቀበሉ /ዶክመንቶች/ እንዲቀበሉ ፣ ሊብሬ እንዲያወጡ ፣ ሰሌዳ እንዲያስለጥፉ

የወካይ ሙሉ ስም

የወካይ ፊርማ

Output copied to clipboard!