Explore a rich collection of Amharic proverbs that reflect the wisdom and cultural heritage of Ethiopia. Our collection includes a wide range of common proverbs, each with its unique meaning and context. You can easily browse the proverbs alphabetically or search for a specific one using your own keywords. Whether you are a language enthusiast, a student of Amharic culture, or simply looking for inspiration, our collection of Amharic proverbs is an excellent resource to explore. Start browsing now and discover the beauty and richness of Amharic language and culture. ሀ ለ ሐ መ ሠ ሰ ሸ ቀ በ ቨ ተ ቸ ኀ ነ ኘ አ ከ ኸ ወ ዐ ዘ ዠ የ ደ ጀ ገ ጠ ጨ ጰ ጸ ፀ ፈ ፐ ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል ሽል አንደሆን ይገፋል ቂጣም እንደሆን ይጠፋል ሽመልና ዘንግ ቂልና በግ ሽማግሌ ሳለ ምክር አይጠፋም ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ ሽማግሌ ካለበት ነገር አይናቅበት ሽማግሌ ካለበት ነገር አይሰረቅ ጎበዝ ካለበት በትር አይነጠቅ ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልመረተ ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልሽተ ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል ሽማግሌና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት ሽሽት ከኡኡታ በፊት ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት እኖር ብዬ አለ ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት ሽንብራ መኖር በመከራ ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ ደገሙትም ገማ Previous12345Next Amharic proverbs contributed by Daniel Aberra