Ethiopian Federal Laws



Title: Definition of Powers and Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia (Amendment)
Proclamation No.: ፭፻፵፮/፲፱፻፺፱
Jurisdiction: ፔዶረል
Law Type: አዋግ
Category: Constitutional Law
Country: Ethiopia 🇪🇹

Format: PDF (Amharic and English) | Text (English | Amharic)


በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ቁጥር ፬፻፸፩/፲፱፻፺፰ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ /፩/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡






  • ፊ. አጭር ርዕስ

    ይህ አዋጅ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር ፭፻፵፮/፲፱፻፺፱” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

  • ፪. ማሻሻያ

    የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፬፻፸፩/፲፱፻፺፰ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡፡

    1. የአዋጁ አንቀጽ ፳፮ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ኣንቀጽ ፳፮ ተተክቷል፡፡
      • "፳፮ የማስታወቂያ ሚኒስቴር

        የማስታወቂያ ሚኒስቴር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፡፡

        1. የመንግሥት ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ሥራን በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፤
        2. የመንግሥት ኢንፎርሜሽን ዋነኛ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፣ በልዩ ልዩ መንገዶች ያሰራጫል፣ በሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የመንግሥትን አቋም ይገልጻል፤
        3. ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉና የአገሪቱን መልካም ገጽታ የሚያጐለብቱ ሁነቶችን ይፈ ጥራል፣ ያስተባብራል፣ ያስተዋው ቃል፣ በነዚህ ተግባራት ላይ የሚያተኩሩ የሚዲያ ፕሮግራሞች እንዲዘጋጁና እንዲሰራ ያደርጋል፣
        4. በመንግሥት ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም በብሔራዊ መግባባትና በገጽታ ግንባታ ሥራዎች ላይ በፌዴራልና በክልል አካላት መካከል የግንኙነት ስርዓት ይዘረጋል፣ ተፈፃሚነቱንም ይከታተላል፤
        5. የሀገር ውስጥና የውጭ ሚዲያ የዕለት ተዕለት ዘገባ አዝማሚያ ክትትልና የከባቢያዊ ሁኔታ ቅኝት ሥራዎችን ያከናውናል፣ ትንተና ያዘጋጃል፣ እንዲሁም የሕዝብ አስተያየት በማሰባሰብና በመተንተን ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፤
        6. ሚዲያዎች ከመንግሥት ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ያስተባብራል፣ ለሚዲያ ኢንፎርሜሽን ጥያቄ አግባብ ባላቸው የመንግሥት አካላት ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ዋና ዋና ሃገራዊ ጉዳዮች፣ ክንውኖችና ሁነቶች ተገቢው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጣቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
        7. በመንግሥት ፖሊሲዎችና በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመስጠትና ግልጽነትን ለመፍጠር ሕዝባዊ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃል፣ ያስተባብሪል፤
        8. ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው እንዲ ያነጋግሩና ተቋማትን፣ ድርጅቶችን፣ ሁነቶችን፣ የሥራ አፈፃፀሞችንና ክንውኖችን እንዲጐበኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
        9. በመንግሥት ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን እንዲሁም በሚዲያ ማስፋፋት ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት የሥልጠናና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞችን በማቀድና በማስተባበር የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያከናውናል፤
        10. አስፈላጊው ሙያዊ ብቃትና ሥነ-ምግባር ያለው የጋዜጠኝነት ሙያ እንዲስፋፋና እንዲዳብር የሚያደርጉ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችንና የቴክኒክ ድጋፎችን ይሰጣል፤
        11. የመንግሥት ፖሊሲዎችን ለማስተዋወቅና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ፕሮዳክሽን ያዘጋጃል፣ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችም እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ ያዘጋጃል፣ ያማክራል፤
        12. የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፎቶግራፍ፣ የኦዲዮቪዲዮ ቀረፃና ህትመት እንዲሁም የአርማና የህትመትዲዛይን እንዲሠራላቸው ሲጠይቁ ያዘጋጃል፣ ያማክራል፤
        13. የሀገሪቱ ሚዲያ በዓይነትም ሆነ በብዛት የሚስፋፋበትንና ዓለም አቀፍ ሥርጭቱ እየሰፋ የሚሄድበትን እንዲሁም ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢ ሕዝቦችና የኅብረተሰብ ክፍሎች ከመንግሥት መረጃ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
        14. የብሮድካስት አገልግሎት ለአገር እድገት አስተዋጽኦ ሊያበረክት በሚችልመልኩ መካሄዱን ያረጋግጣል፣ በብሮድካስት ማስፋፋት ሥራ ፈቃድሰጪው አካል በሕጉ መሠረት መሰራቱን ይቆጣጠራል፤
        15. ሥርጭታቸው በአንድ ክልል ውስጥ ከተወሰኑት በስተቀር የንግድ ፕሬሶችን ይመዘግባል፣ የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፣ እንዲሁም የንግድ አላማ ለሌላቸው ፕሬሶች ፈቃድ ይሰጣል፣ በሕግ መሠረት መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤
        16. በሀገሪቱ ውስጥ በቋሚ የዜና ወኪልነት ለሚመደቡ የውጪ አገር የዜና ወኪሎች ፈቃድ ይሰጣል፣ ሕግ አክብረው መስራታቸውን ያረጋግጣል፤
        17. ለጊዜያዊ ሥራ ለሚመጡ የውጭ አገር ጋዜጠኞችና ፊልም አንሺዎች ፈቃድ ይሰጣል፣ ሕግ አክብረው መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤
        18. የማስታወቂያ ሥራ ሕግን ተከትሎና ለሀገር ልማት አስተዋጽኦ ሊያደርግ በሚችልበት አቅጣጫ ስለመከናወኑ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
        19. የተለየ ሙያ በሚጠይቁ የሥራ መደቦች የሚመደቡ ሠራተኞችን ከመንግሥት በሚፈቀድ የደመወዝ ስኬል መሠረት እንዲሁም ሌሎች ሠራተኞችን በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ መሠረት ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፤
        20. በሀገር ውስጥ የዜና ሥራ የሚሰሩቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ይኖሩታል፣ እንደአስፈላጊነቱም በውጭ ሀገር ቅርንጫፎች እንዲኖሩት ይደረጋል፤
        21. በመንግሥት ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን፣ በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች እንዲሁም በፖሊሲ ተግባራ ላይ ጥናት ያካሂዳል፣ ያስተባብራል፣ የጥናቱ ውጤቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትንና ጥቅም ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡"
        22. ለሚሰጣቸው አገልግሎት በሕግ መሠረት ክፍያ ይሰበስባል
    2. ከአዋጁ አንቀጽ ፴፬ ንዑስ አንቀጽ /፩/ ተራ ፊደል /ሠ/ ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል /ረ/ ተጨምሯል፡፡
      1. "ረ/ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፲፭/፲፱፻፹፯/ እንደተሻሻለ/፡፡"
    3. ከአዋጁ አንቀጽ ፴፭ ንዑስ አንቀጽ /፯/ ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ /፰/ ተጨምሯል፡፡
      1. "፰/ በአዋጅ ቁጥር ፩፻፲፭/፲፱፻፹፯ እንደተሻሻለው ተቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለማስታወቂያ ሚኒስቴር ተላልፈዋል፡፡"
  • ፫. የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች

    የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በአዲስ አደረጃጀት እስከሚጠቃለል ድረስ ተግባርና ሃላፊነቱን በአዋጅ ቁጥር ፩፻፲፭/፲፱፻፹፯ መሠረት እየተወጣይቆያል፡፡

  • ፬. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ

    ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ነሐሴ ፲፭ ቀን ፲፱፻፺፱ ዓ.ም

ግርማ ወልደጊዮርጊስ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት





Output copied to clipboard!